የአድራሽ አጋር አሽከርካሪዎች
ለመመዝገብ ሲመጡ እነዚህን በሙሉ አሟልተው ይቅረቡ
እባክዎ ከመምጣትዎ በፊት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሰነዶች እና ፎቶዎች በሙሉ ማዘጋጀትዎን ያረጋግጡ።
የአሽከርካሪው መታወቂያ እና መንጃ ፈቃድ
ብሔራዊ መታወቂያ (National ID)
ዋናውን መታወቂያ ይዘው መቅረብ ወይም የፊትና የኋላ ገጹን በግልጽ የሚያሳይ ስካን(Scan) ማቅረብ ይቻላል።
የመንጃ ፈቃድ
የታደሰ መሆን አለበት። ዋናውን መንጃ ፈቃድ ይዘው መቅረብ ወይም የፊተኛውን ገጽ ብቻ በግልጽ የሚያሳይ ስካን(Scan) የተደረገ ኮፒ ማቅረብ ይቻላል።
ባለቤትነት እና የደኅንነት ሰነዶች
የተሽከርካሪ ባለቤትነት ማረጋገጫ (ሊብሬ)
ዋናውን ሊብሬ ይዘው መቅረብ ወይም በግልጽ የተቃኘ (Scanned) ኮፒ ማቅረብ።
የመድን ዋስትና (ኢንሹራንስ)
በቅርቡ የታደሰ እና አስተማማኝ ጊዜ ያለው (Updated) መሆን አለበት።
ዓመታዊ የተሽከርካሪ ምርመራ (ቦሎ)
የአሁኑን የቦሎ ስቲከር የሚያሳይ ግልጽ ፎቶ።
ሊነሱ የሚገባቸው የተሽከርካሪ ፎቶዎች
የሚመዘግቡት መኪና ንጹሕ መሆኑን ያረጋግጡ እና የሚከተሉትን 4 የተሽከርካሪ ፎቶዎች በግልጽ አስነስተው ይዘው ይምጡ፦
የመኪናው የፊት ገጽ ፎቶ
ታርጋውና ሙሉ የፊቱ አካል በግልጽ የሚታይ
የመኪናው የጀርባ ገጽ ፎቶ
ታርጋውና ሙሉ የኋላው አካል በግልጽ የሚታይ
የዳሽቦርድ ፎቶ
የፊት ፓነል በግልጽ የሚታይበት
የተሳፋሪ ወንበር ፎቶ
የውስጠኛው ክፍል ንጽሕ በሆነ ሁኔታ የሚታይበት
ማስጠንቀቂያ
ያዘጋጇቸው የፎቶ እና ሰነዶች ላይ ያሉ ጽሑፎች፣ ቀኖች እና ቁጥሮች በሙሉ በትክክል የሚነበቡና የማይደብዝዙ መሆናቸውን ከመምጣትዎ በፊት ደግመው ያረጋግጡ!